Fana: At a Speed of Life!

በመቐለ ዳግም ትምህርት በመጀመሩ መደሰታቸውን ተማሪዎች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል መቐለከተማ የመማር ማስተማር ሂደቱ ዳግም በመጀመሩ መደሰታቸውን ተማሪዎች ገለጹ፡፡

የጋዜጠኞች ቡድን በመቐለ የፈለገ ህይወት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና በአጼ ዮሐንስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት የመማር ማስተማር ሂደቱን ቃኝቷል፡፡

በከተማዋ ተማሪዎች መደበኛ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ መሆናቸውንም ተመልክቷል፡፡

በፈለገ ህይወት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሰጡት አስተያየት ረጅም ጊዜ በቤት ውስጥ አሳልፈው ቆይተው አሁን ላይ ትምህርት በመጀመራቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

የመማር ማስተማር ሂደቱ ሳይጀመር ያሳለፉትን ጊዜ ለማካካስም ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

ወደ ትምህርት ቤት ያልመጡ ሌሎች ተማሪዎችም ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ተማሪዎቹ ትምህርት የሁሉ ነገር መሰረት በመሆኑ በየትኛውም አጋጣሚ በመማር ተስፋ እንዲኖረን ማድረግ አለብን ብለዋል።

“ሁላችንም ለመማር ዝግጁ መሆን ይኖርብናል ወላጆችም ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላክ ይኖርባቸዋል”ብለዋል ተማሪዎቹ በአስተያየታቸው።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኢንጅነር አስቴር ይትባረክ ÷በከተማዋ የመንግሥትና የግል ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራ መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ ተፈናቃዮች ባሉባቸው አካባቢዎች ትምህርት እንደሚጀመርም ተናግረው፤ወደ ትምህርት ገበታ ያልተመለሱ ተማሪዎችን ወላጆች ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩም ምክትል ኃላፊዋ ጠይቀዋል፡፡

የአጼ ዮሐንስ 4ኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ 12ኛ ክፍል ተማሪዎችም ብሄራዊ ፈተናን ለመውሰድ ቅጽ ሲሞሉ   የኢዜአ ሪፖርተር በስፍራው በመዘዋወር ተመልክቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.