Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን በዘር በሀይማኖትና በጎሳ ሳይከፋፋሉ በጋራ የውጭ ተፅዕኖን መቋቋም እንደሚገባቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ኢትዮጵያውያን በዘር በሀይማኖትና በጎሳ ሳይከፋፋሉ በአንድነት ቆመው የውጭ ሀገራትን ተፅዕኖ መቋቋም እንደሚገባቸው ገለጸ።

ጉባኤው በሰላም በአብሮነትና በግጭት አያያዝና አፈታት ላይ ያተኮረ ምክክር ዛሬ በጅማ ከተማ አካሂዷል።

በጉባኤው ላይ የሀይማኖት አባቶችናና የተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል።

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሀፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ “ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከውጭም ከውስጥም እየተፈተነች ያለችበት ጊዜ በመሆኑ በዘር በሀይማኖት ሳንከፋፈል በወንድማማችነት ስሜት በጋራ በመቆም ተፅዕኖዎችን መቋቋም ያስፈልጋል” ብለዋል።

የኦሮሚያ እስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሼህ አብዱልሀሚድ አህመድ በበኩላቸው ኢትዮጵያውያን ከምንም ጊዜ በላይ ሀገርን የሚያስቀድሙበት ወቅት መሆኑን ጠቁመው የውስጥ ችግሮች ቢኖሩ እንኳን በመነጋገር መፍታት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

በበሪሳ ሃይለማርያም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.