Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ የቴክኒክ ትምህርትና ስልጠና ልህቀት ማዕከል ሊገነባ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ የቴክኒክ ትምህርትና ስልጠና ልህቀት ማዕከል በ12 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ የአሜሪካን ዶላር ሊገነባ ነው፡፡

የልህቀት ማዕከሉን ለመገንባት  የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠ ሲሆን በመርሃ ግብሩ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የኮምልቻ ከተማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በምስራቅ አፍሪካ 7 የልህቀት ማዕከል ተብለው ከተመረጡ አንዱ እንደሆነ የገለፁት ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ኮሌጁ ወደፊት ተወዳዳሪና ብቁ የልህቀት ማዕከል እንዲሆን ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በቅርበት እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡

በኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ የቴክኒክ ትምህርትና ስልጠና ልህቀት ማእከል ፕሮጀክት የሚገነባው በዓለም ባንክ በተገኘ 12 ሚሊየን 850 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የገንዘብ ድጋፍና ብድር ነው፡፡

ፕሮጀክቱ ለአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ትኩረት በመስጠት ውጤታማ ሥራዎችን ለማከናወን ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በይከበር አለሙ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

በሶስት ቋንቋዎች የተሰራ ፊልም ለእይታ ሊቀርብ ነው

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.