Fana: At a Speed of Life!

በ124 ሚሊየን ብር ማስፋፊያ የተደረገበት የጦር ሃይሎች ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ124 ሚሊየን ብር የማስፋፊያ ስራ የተሰራለት የጦር ሃይሎች ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አግልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር ቀንአ ያደታ በሪፎርም ስራው በሆስፒታሉ የተሰሩ ስራዎችን በመጎብኘት የሆስፒታሉን አገልገሎት በይፋ አስጀምረዋል፡፡

ሚኒስትሩ የጦር ሃይሎች ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በትግራይ በነበረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ላይ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋነናአቅርበዋል፡፡

በሕግ ማስከበር ተልዕኮው ከሰራዊቱ ጎን በመሆን ድጋፍ ላደረጉ ተቋማት እና ግለሰቦች የምስጋና እና የእውቅና ሥነ ሥርዓትም ተካሂዷል፡፡

በጦር ሀይሎች ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔቫላይዝድ ሆስፒታል የላቀ ስራ ለሰሩ የሆስፒታሉ ሰራተኞችም የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

በተሰራው የለውጥ ስራ የእናቶች እና ህጻናት ሕክምና ክፍል ተገንብቶ ስራ መጀመሩን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.