Fana: At a Speed of Life!

ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ከጠ/ሚ ዐቢይ ለኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የተላከ ደብዳቤ አደረሱ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩቴ የተላከ ደብዳቤን አደረሱ፡፡

ደብዳቤውን ለሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና የውጭ ንግድ እና ልማት ትብብር ሚኒስትር ሲግሪድ ካግ አስረክበዋል፡፡

በዚህ ወቅትም ከሚኒስትሯ ጋር በተለያዩ ጉደዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

በውይይታቸው ወቅትም በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ፣ በመጪው ሃገራዊ ምርጫ፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድር እና በኢትዮ ሱዳን የድንበር ውዝግብ ዙሪያ መምከራቸውንም ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.