Fana: At a Speed of Life!

በባህርዳር ከተማ በ400 ሚሊየን ብር ወጪ የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህርዳር ከተማ በ400 ሚሊየን ብር ወጪ የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ተጀመረ፡፡

ግንባታው የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉን ጨምሮ ሌሎች የከተማና የክልል አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት ዛሬ ተጀምሯል።

ግንባታዎቹ ሁለት አዳዲስ የአስፓልት መንገዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡

በአፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ ከዳያስፖራ አስፓልት መገንጠያ እስከ ዘንዘልማ ዋናው አስፓልት 3 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትርና በዳግማዊ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ከባለእግዚአብሔር አዲስ አስፓልት እስከ ልደታ ታክሲ መገንጠያ 1 ኪሎ ሚትር በድምሩ 4 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው ናቸው፡፡

ለመንገዶቹ ግንባታ 400 ሚሊየን ብር ወጪ ይደረጋል መባሉን ከባህር ዳር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.