Fana: At a Speed of Life!

በዞን ደረጃ የሚዘጋጀው ታላቁ ሩጫ በወላይታ   ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በዞን ደረጃ የሚዘጋጀው ታላቁ ሩጫ በወላይታ ለወላይታ 6ኛው ዙር “ስፖርት ለሁለንተናዊ ብልፅግና”በሚል መሪ ቃል ሊካሄድ ነው።

የሩጫ ውድድ ሩ የተዘጋጀው ስፖርት ለሠላም፣ ለልማት፣ ለአብሮነትና ለለውጥ ያለውን ፋይዳ በመገንዘብና ከዘርፉ የሚገኘውን ከፍተኛ ጥቅም ተቋዳሽ ለመሆን በማሰብ መሆኑ ተገልጿል ።

የወላይታ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ምክትል ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አኩዬ ጌካ ይህንን መርሐ ግብር በወላይታ ዞን ስፖርት ምክር ቤት ሲያዘጋጅ ከ21 ሺህ በላይ ተሳታፊዎችን ለማስተናገድ ማቀዱን ገልፀዋል።

የአካባቢ ሰላምና እድገት ለማስጠበቅ ስፖርት ትልቅ ሚና አለው ያሉት ኃላፊው÷ በተለይም በአትሌቲክስ ዘርፍ ከአካባቢው ታዳጊዎች እንዲወጡ እድል ለመፍጠር ይህ ውድድር ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።

መርሐ ግብሩ በሠላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የጠቆሙት አቶ አኩዬ ጌካ ÷ በውድድሩ የተሳተፉ ሁሉ የሠላምና የለውጥ አሸናፊዎች ናቸውና ሁላችሁም  ኑ ለሠላም በፍቅር እንሩጥ ብለዋል።

ሰኔ 5  ቀን 2013 ዓ.ም የሚካሄደው ይህ ሩጫ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከፍሬው አልታዬ አደባባይ ወይም ከአዲሱ የኃይሌ ገብረስላሴ ሪዞርት ፊትለፊት እስከ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ  መሆኑም ተመላክቷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራልና የክልል የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ስፖርት ፌዴሬሽን አመራሮችና ሌሎች የሚመለከታቸውና ተጋባዥ እንግዶች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

በመለሰ ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.