Fana: At a Speed of Life!

13ኛው የፖሊስ ኮሚሽነሮች ጉባኤ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅግጅጋ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 13ኛው የፌደራል፣የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የፖሊስ ኮሚሽነሮች ጉባኤ ተጠናቋል።
ጉባዔው ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ነው የተጠናቀቀው።
በአቋም መግለጫው ከተቀመጡት ነጥቦች መካከል በሀገራዊ የፖሊስ ተቋማት ሪፎርም የተጀመሩ ለውጦችን አጠናክሮ ማስቀጠል፣ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር ጠንካራ ግንኙነት ማጠናከር፣ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ፖሊስ ገለልተኛ ሆኖ መስራት ፣ህዝብና መንግስት ከድህነት ለመውጣት የጀመሩትን የታላቁን ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከግብ እንዲደርስ የትኛውንም መስዋዕትነት መክፈል የሚሉ ይገኙበታል።
በተጨማሪም የፌደራል፤ የክልልና የከተማ አስተዳደር ፖሊሶች ውስጣዊ አንድነታንን በማጠናከር በጋራ በኢትዮጵያ ላይ የሚቃጣውን የትኛውንም አይነት የወንጀል ተግባር መከላከል፣በምርጫው ወቅትና ከምርጫው በኋላ ምንም ዓይነት ህግወጥ እንቅስቃሴ በየትኛው አካባቢ እንዳይኖር ጠንካራ ፖሊሳዊ መረጃ ልውውጥ ስርዓት በመዘርጋት የሚለው በአቋም መግለጫው ከተካተቱት ነጥቦች መሃል መሆኑን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.