Fana: At a Speed of Life!

የፒኮክ መናፈሻ መካነ እንስሳት ፓርክ በይፋ ተመርቆ ተከፈተ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፒኮክ መናፈሻ አዲስ የመካነ እንስሳት (ዙ ፓርክ) በይፋ ተመርቆ ተከፈተ ።

ፓርኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማዋ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታአቶ ጌታቸው ኃይለማርያም ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ባለድርሻ አካላትና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት ተመርቆ በይፋ ስራ ጀምሯል ።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የማዕከሉ በዚህ ደረጃ ከፍ ባለ የስነ ምህዳር እና የመካነ እንስሳት ማዕከልነት ደረጃ መገንባቱ ከተማዋን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ለተያዘው እቅድ ማሳያ ጅማሮ ነው ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በቀጣይም ለማዕከሉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ወይዘሮ አዳነች፥ በማዕከሉ ግንባታ ወቅት ተሳታፊ ለነበሩ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በፓርኩ ባለ ጥቁር ጎፈር አንበሳ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ፣ ሚዳቋና ሌሎች ከ12 በላይ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ከ53 በላይ እንስሳት እንደሚገኙ ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፓርኩ በመከላከያ ሚኒስቴር ኮንስትራክሽን አማካኝነት የተገነባ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.