Fana: At a Speed of Life!

ተሽከርካሪ የዘረፉ 12 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሸዋ ዞን ተሽከርካሪ የዘረፉ 12 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ።
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ሃላፊ ኮማንደር አስቻለው ዓለሙ እንደገለፁት በዞኑ በአዳሚ ቱሉ ጅዱ ኮምቦልቻና ሊበን ወረዳዎች የተሽከርካሪ ዘረፋ ወንጀል የፈጸሙ 12 ግለቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ግለሰቦቹ ንብረትነቱ የሰላም ውሃ ማምረቻ ፋብሪካ የሆኑ አንድ ኤፍ ኤስ አርና አንድ አይሱዙ እንዲሁም አንድ ሲኖ ትራክ በድምሩ ሶስት ተሽከርካሪዎችን ሚያዝያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ጨለማን ተገን በማድረግ መዝረፋቸውን ገልጸዋል።
ዘራፊዎቹ የሀሰት ሰሌዳ ቁጥር በተለጠፈባቸው ሁለት ቪትስ ተሽከርካሪዎችና በጦር መሳሪያ በመታገዝ የተሽከርካሪ ዝርፊያውን መፈጸማቸውን ተናግረዋል።
በተለይም የኤፍ ኤስ አር አሽከርካሪውን ዛፍ ላይ አስረው የዘረፏቸውን ተሽከርካሪዎች ይዘው መሰወራቸውን ኮማንደር አስቻለው ተናግረዋል።
የዞኑ ፖሊስ መምሪያም ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪ ዘራፊዎቹ የዘረፋ ወንጀሉን ለመፈጸም ሲጠቀሙባቸው ከነበሩ ተሽከርካሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.