Fana: At a Speed of Life!

በመቐለ ከተማ የሚገኙ የጤና ተቋማት በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል በመቐለ ከተማ የሚገኙ የጤና ተቋማት በሙሉ አቅማቸው የህክምና አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡
በክልሉ ከ60 በላይ ተንቀሳቀሽ ክሊኒኮች ተዘዋውረው የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
መቐለ የሚገኘው የጋዜጠኞች ቡድን በዛሬው ዕለት የካቲት 11 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልንና ዓዲ ሽምዱሑን ጤና ጣቢያ የተባሉ የጤና ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥን ጎብኝቷል፡፡
የየካቲት 11 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ሲስተር ፍሬወይኒ ኃይለማርያም እንዳሉት ሆስፒታሉ በሙሉ አቅሙ የህክምና አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
ሆኖም ተገልጋዮች ከዚህ ቀደም በሆስፒታሉ ይታከሙ ከነበሩ በእጥፍ መጨመራቸውን ተናግረው ይህ የታካሚዎች መብዛትም በሆስፒታሉ የመድሃኒትና የሰው ሃይል እጥረት እንዲገጥም ምክንያት መሆኑም ጠቁመዋል፡፡
የዓዲሽምዱሑን ጤና ጣቢያ ዳይሬክተር አቶ ጀማል ነፊስን በሰጡት አስተያየትም ጤና ጣቢያው በሙሉ አቅሙ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ዳይሬክተሮቹ በሰጡት አስተያየትም አሁን ላይ በክልሉ እየተከሰቱ የሚገኙ የኮሌራ እና ኮቪድ 19 ጨምሮ ሌሎች የህክምና አገልግሎቶችን በተሳካ መልኩ መስጠት የበጀት አለመለቀቅ ችግር እንዳለባቸውም ተናግረዋል፡፡
በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የድንገተኛ ህክምና የፈውስና ተሃድሶ የሥራ ሂደት አስተባባሪ ዶክተር አቤኔዘር ዕጸድንግል በበኩላቸው በመቐለ አምስት ሆስፒታሎችና 11 ጤና ጣቢያዎች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡
የጤና ተቋማቱ በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ እንዲገቡም የጤና ሚኒስቴር እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ሚና ከፍተኛ እንደነበር የገለፁ ሲሆን የጋዜጠኞች ቡድንም ባደረገው ቅኝት የጤና ተቋማቱ መደበኛ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን መመልከቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.