Fana: At a Speed of Life!

በእንግሊዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ሰልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አንዳንድ የቡድን 7 አባል ሀገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትን እንደሚቃወሙ በእንግሊዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ገለጹ፡፡
”ለኢትዮጵያ ዘብ እንቁም” በሚል መሪ ቃል የዩናየትድ ኪንግደም ግብረኃይል ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ማኅበረሰብ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት ሰልፍ ላይ የቡድን 7 አባል ሀገራት መሪዎች ስብሰባ ላይ ድምፃቸውን ያሰሙት ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን የሀገራት ሉዓላዊ ስልጣን ሊከበር ይገባል ብለዋል፡፡
ለኢትዮጵያ ዘብ እንቁም ግብረኃይል አስተባባሪ ዘላለም ተሰማ ÷ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ጫና ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ለአፍሪካ ቀንድም ሆነ ለምዕራቡ ዓለም የሚበጅ አይደለም ነው ያሉት፡፡
የኢትዮጵያ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት ሊከበር ይገባዋል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያን እጣ ፈንታ የሚወስነው የኢትዮጵያ ሕዝብ በመሆኑ በሌሎች ጣልቃ ገብነት ሰላሙን ለማወክ የሚደረገውን ጥረት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ያለው ኢትዮጵያዊ በሕብረት በመቆም ሊታገለው እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
በጋራ የመከባበር መርህ ላይ ተመስርቶ ለኢትዮጵያ የሚደረግ ድጋፍ ለሁሉም የሚጠቅም በመሆኑ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
በድጋፍ ስም የሚደረግ ጫና እና እጅ መጠምዘዝ ግን የኢትዮጵያን ታሪክ ካለማወቅ የመነጨ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ አበበ ቶሎሳ ÷ በቡድን ሰባት ውስጥ ያሉ አንዳንድ ሀገሮች በሰብዓዊነት ሽፋን የኢትዮጵያን አንድነት፣ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት በሚጋፋ መልኩ ኢትዮጵያን ለማዳከም የሚያደርጉት አፍራሽ ተግባርን እንዲያቆሙ ጠይቀዋል።
ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ ቶማስ ሀብተወልድ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለው ጫና መልካም ስሟን የማጉደፍ ዘመቻ እና የሐሰት መረጃ ለማንም የሚጠቅም ባለመሆኑ አንዳንድ የቡድን 7 አባል ሀገራት በተሳሳተ መረጃ በኢትዮጵያ ላይ ሊሳርፉ የሚፈልገውን ተጽእኖ እንደማይቀበሉ አመልክተዋል፡፡
ሰልፈኞቹ የህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌት የተሳካ እንዲሆን ቦንድ ከመግዛት በተጨማሪ የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ ሥራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
ሀገራዊ ምርጫው የተሳካ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ሚና እንደሚጫወቱ መግለጻቸውን ከለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያደረሰን ነው ሲል አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+3
0
People Reached
294
Engagements
Boost Post
256
18 Comments
20 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.