Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ የተገነባው 132/33 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ ከ65 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የነጆ ባለ 132/33 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ተመርቋል።
በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን፣ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻን ጨምሮ የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ አባ ገዳዎችና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል፡፡
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ÷ የማከፋፈያ ጣቢያው መገንባት ባለሃብቶች እና ኢንቨስተሮች በአካባቢው በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ እንዲሳተፉ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።
የኤሌክትሪክ ኃይል ለአንድ ሀገር ሁሉ ነገር በመሆኑ በቀጣይ በክልሉ የኃይል ተደራሽነትን ለማስፋፋት ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራል ብለዋል።
ባለሀብቶች የተፈጠረላቸውን ዕድል በመጠቀም በግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች እና በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በመሳተፍ አካባቢያቸውን ለመቀየር ጠንክረው እንዲሰሩ አሳስበዋል።
የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ በታዳሽ የኃይል ምንጮች ላይ ትኩረት በማድረግ ለሀገር ዕድገት እና ለአህጉራዊ ትስስር መሠረት የሚሆን አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ እየሠራች ትገኛለች ብለዋል።
በሀገሪቱ እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት እና የመነጨውን ኃይል ለተጠቃሚው ፍትሐዊ በሆነ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ የማስተላለፊያ መስመሮች እና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ ላይ ትኩረት ተሠጥቶ እየተሠራ ነው ብለዋል።
ሚኒስትሩ አያይዘውም ማከፋፈያ ጣቢያው 40 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃያል የማስተላለፍ አቅም እንዳለው ጠቁመው÷ ጣቢያው ለነጆ ከተማ እና አካባቢው ማኅበረሰብ የኤሌክትሪክ ኃይል ከማቅረብ ባለፈ በአካባቢው የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋት ፋይዳው የጎላ ሲሉ ገልጸዋል።
ባለሀብቶች በአካባቢው የሚገኙ የተፈጥሮ ኃብቶችን በአግባቡ በመጠቀም አካባቢያቸውን እንዲያለሙም ዶክተር ስለሺ ጥሪ አቅርበዋል።
ማከፋፈያ ጣቢያው 50 ሜጋ ቮልት አምፔር ትራንስፎርመር እና አራት ባለ 33 ኪሎ ቮልት ወጭ መስመሮች ያሉት ሲሆን የተገነባውም በተቋሙ የትራንስሚሽን እና ሰብስቴሽን ኮንስትራክሽን የራስ ኃይል ቢሮ ነው።
ሙሉ ወጪውም በኢትዮጵያ መንግሥት የተሸፈነ መሆኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People Reached
1
Engagement
Boost Post
1
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.