Fana: At a Speed of Life!

የመንገድ ደህንነት በስርዓተ ትምህርት ውስጥ ሊካተት ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንገድ ደህንነት ስርዓተ ትምህርትን በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ የማከተት መርሃ ግብር በስካይ ላይት ሆቴል በመካሄድ ላይ ነው።

መርሃ ግብሩ “የመንገድ ደህንነት ትምህርት ለሁሉም”  በሚል መሪ ሃሳብ  ነው እየተካሄደ ያለው።

የመንገድ ደህንነት ስርዓተ ትምህርት ከቅደመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል እንዲሁም በጎልማሶች ትምህርት እንዲካተት ተደርጎ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተቀረፀ ሲሆን በ2014 ወደ ስራ ይገባል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ÷ በ 2014 ወደ ትግበራ የሚገባው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት፣ የትምህርት ጥራትን ታሳቢ ያደረገና ባለፉት አመታት የታዩ ችግሮችን ነቅሶ ያወጣ መሆኑን ተናግረዋል።

በቀጣይ አመት ከ50 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የመንገድ ደህንነት ትምህርት ተግባራዊ እንደሚደረግ የገለፁት ሚኒስትሩ÷ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የትራፊክ ደህንነት ትምህርት በስርዓተ ትምህርት ውስጥ መካተቱ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን አደጋ እንዲቀንስ ያስችላል ብለዋል ።

የትራንስፖርት ሚነስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በበኩላቸው÷ ደህንነቱ የተጠበቀ የመንገድ አጠቃቀምን ባህል ለማድረግና የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ሚኒስቴሩ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን ገለፀዋል።

የመንገድ ደህንነት ትምህርት በስርዓተ ትምህርት ውስጥ መካተቱ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ከማምጣቱም በላይ የመንገድ አጠቃቀምን ባህል ለማድረግ የሚረዳ መሆኑን ሚኒስትሯ ገልፀዋል።

ስርዓተ ትምህርቱ ዜጎች የመንገድ ትራፊክ ህግና ደንብን በአግባቡ አውቀው ተግባራዊ እንዲያደርጉ እና ሌሎችንም እንዲያሳውቁ እድል እንደሚፈጥርም ተገልጿል።

በዝግጅቱም የመንገድ ደህንነት ትምህርትን ለማስተማር  የሚያስችሉ ቋሳቁሶችን ትምህርት ሚኒስቴር ከትራንስፓርት ሚኒስቴር ተረክቧል።

በ2014 ተግባራዊ በሚደረገው የመንገድ ደህንነት ትምህርት ላይ በ 11 የትምህርት አይነቶች የመንገድ ደህንነት ትምህርት የሚተገበር ሲሆን  ከ34 ሚሊየን  በላይ ተማሪዎችን ለመድረስ እንደሚያስችል ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.