Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባን የኢትዮጵያ ብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ማንም የሚያስቆመን አካል የለም – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባን የኢትዮጵያ ብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ማንም የሚመልሰን፤ የሚያስቆመን አካል የለም  ሲሉ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ  ይህንን የተናገሩት ÷የአዲስ አበባ ከተማ ኮንስትራክሽን ቢሮ በበጀት ዓመቱ ባከናወናቸውን የልማት ስራዎች አስተዋጽኦ ላበረከቱ ስራ ተቋራጮች እና የኮንስትራክሽን ዘርፍ ባለድርሻ አካላት የምስጋና እና የእውቅና መርሐግብር በተካሄደበት ወቅት ነው ።

ምክትል ከንቲባዋ በእውቅና መርሐግብር ላይ እንዳስታወቁት ÷ በበጀት ዓመቱ በከተማዋ ከ7 በላይ ሜጋ  ፕሮጀክቶች ተጀምረው በትላንትናው ዕለት ከማዘጋጃ ቤት -የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት በይፋ መመረቁን አስታውሰዋል።

በአጠቃላይ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከ2ሺህ 500 በላይ ፕሮጀክቶች መጠናቀቁንም ነው የገለጹት ።

ፕሮጀክቶቹ የከተማዋን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ከማሳደግ ባለፈ ገጽታን በመቀየር በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ብለዋል ምክትል ከንቲባዋ።

በበጀት ዓመቱ በጠቅላላው ከተያዘው 61 ቢሊየን ብር ከ33 ቢሊየን ብር ለልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች መዋሉን ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል ።

በዚህም ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረጉ እና የመጣውን  ለውጥ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል ።

በበጀት ዓመቱም ለነዚህ ፕሮጀክቶች መጠናቀቅ የበኩላቸውን ሚና ለተወጡ ስራ ተቋራጮች በተለይ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን እና የኮንስትራክሽን ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ሊመሰገኑ እና ሊበረታቱ እንደሚገባም ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች መግለጻቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.