Fana: At a Speed of Life!

የስማርት ምሰሶ ቴክኖሎጂ ምንድነው?

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የስማርት ምሰሶ ቴክኖሎጂ ስማርት ከተሞችን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት አንዱ ግብዓት መሆኑን ስማርት ሲቲ ፕረስ ያትታል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ኢትዮ ቴሌኮም ደምበኞች የዳታ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸውን ስማርት ምሰሶ በእንጦጦ ፓርክ ማስመረቁ ይታወሳል፡፡

የስማርት ምሰሶ ቴክኖሎጂ ከተለመዱት የመንገድ ዳር ምሰሶዎች ጋር የሚመሳሰል ነገር ግን ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን የያዘ ነው፡፡

ከሚሰጠው አገልግሎት መካከል አንዱ፥ ሰፊ አካባቢን መሸፈን የሚችል እጅግ ፈጣን የአራተኛ ትውልድ (4ጂ)፣ አምስተኛ ትውልድ ( 5ጂ) እና የዋይፋይ አገልግሎት ይሰጣል፡፡

ሌላው መኪና እና ታርጋን በቀላሉ መለየት የሚችሉ፣ የፊት ገፅታ ልየታን የሚያከናውኑ፣ ከፍተኛ የሆነ የቀለም ጥራት እና አጉልቶ የማሳየት አቅም ያላቸው የደህንነት ካሜራዎች ይኖሩታል፡፡

በተጨማሪም የአየር እና የድምፅ ብክለትን የሚለዩ፣ አደጋዎችን እና ወንጀሎችን በፍጥነት ለይቶ በመጠቆም የድንገተኛ ጊዜ ምላሽ አሰጣጡን የሚያቀላጥፉ መጠቆሚያዎችን ይይዛል፡፡

እንዲሁም የመንገድ መጨናነቅ እና አደጋን የመሰሉ እንዲሁም ሌሎች የድንገተኛ ጊዜ መልዕክቶች የሚሰራጩበት ዲጂታል ስክሪንም የሚኖረው ይሆናል፡፡

የስማርት ምሰሶ አገልግሎቶች በዚህ ብቻ የተገደበ ሳይሆን “ሁሉን በአንድ” በሚለው የቴክኖሎጂው መርህ መሰረት ሰዎች ከያዙት መሳሪያ ጋር በቀላሉ ተናቦ ለሌሎች አገልግሎቶች እንደሚውል ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.