Fana: At a Speed of Life!

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የፖለቲካ ፓርቲዎችን የማጠቃለያ ክርክር አካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በመጋበዝ ሲያደርግ የነበረውን የማጠቃለያ ክርክር አካሄደ፡፡
ጣቢያው የፖለቲካ ፓርቲዎችን በመጋበዝ ለዘጠኝ ጊዜ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ክርክር እንዲካሄድ አድርጓል፡፡
በዚህም 11 ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች አማራጭ ፖሊሲ እና አማራጭ ሀሳቦቻቸውን ለህዝቡ እንዲያደርሱ ለማድረግ ጥረት ተደርጓል፡፡
በአንድነት ፓርክ በተካሄደውና በመጨረሻው የማጠቃለያ የክርክር መርሀግብር ላይም አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀሳባቸውን እና አማራጭ ፖሊሲዎቻቸውን በማቅረብ ተከራክረዋል፡፡
ከቀደምቶቹ ክርክሮች በተለየ መልኩ በዚህ በመጨረሻው ክርክር ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫውን ቢያሸንፉ የሚተገብሯቸውን ቀዳሚ ሁለት አጀንዳዎች አቅርበዋል፡፡
ከአማራጭ ፖሊሲዎቻቸው ላይ ከመከራከር ባለፈ ከምርጫ በኋላ ቢመረጡም ባይመረጡም የህዝብን ውሳኔ ለማክበር ባላቸው ቁርጠኝነት ላይም ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህ የማጠቃለያ ክርክር ላይ አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም የብልጽግና ፓርቲ፣ ኢዜማ ፓርቲ፣ ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ፣ ህብር ኢትዮጵያ ፓርቲ እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ፓርቲዎች ተካፋዮች ሆነዋል፡፡
ፓርቲዎቹ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮሬፖሬት አማራጫቸውን ለህዝብ እንዲያቀርቡ በገለልተኝነት ከአንድ የመገናኛ ብዙሃን የሚጠበቅን ሀላፊነት መወጣቱን በመጥቀስ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በለይኩን ዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.