Fana: At a Speed of Life!

በመቐለ ከተማ ሁለተኛ ዙር የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል መንግስት ከተራድኦ ድርጅቶች ጋር በመሆን ያቀረቡት ስንዴ፣ ዘይትና አተር በትግራይ ተራድኦ ድርጅት በኩል ለተረጂዎች እየተከፉፈለ ነው።

እርዳታው በመቐለ ከተማ ለሚገኙ 379 ሺህ 946 ተፈናቃይና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ተደራሽ የሚሆን ነው ተብሏል።

በመቐለ ከተማ በሰባት ክፍለ ከተሞች በፈረንጆቹ 2020 በጀትን ታሳቢ ያደረገ ከሁለት ወር በፊት ድጋፍ የተደረገ ሲሆን÷ አሁን እየተሰጠ ያለው በየወሩ የሚቀጥልና የ2021 በጀት ነው ተብሏል።

ፉና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ድጋፍ እየተሰጠ ካለባቸው መካከል በሀድነት ክፍለ ከተማ ተገኝቶ ምልከታ ያደረገ ሲሆን÷ ለተረጂዎቹ ስንዴ፣ አተርና ዘይት እየተከፉፈለ መሆኑን አረጋግጧል።


በትግራይ ተራድኦ ድርጅት የመቐለ ከተማ የሀድነት ክፍለ ከተማ አስተባባሪ አቶ ባራኪ ተክሌ ከተማዋ ወደ ቀድሞ ሰላሟ እየተመለሰች በመሆኑ እርዳታውን በትክክል ድጋፍ ለሚገባቸው ዜጎች ለማድረስ ረድቶናል ብለዋል።

ድጋፉን በተሽከርካሪ ከማከፉፈል አሁን በየማእከላቱ በሚገኙ መጋዘኖች ተራግፎ በቀጥታ ለተረጂዎቹ እንዲደርሳቸው ማድረግ በመቻሉ በየወሩ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።

የድጋፉ ተጠቃሚዎች በበኩላቸው ቢዘገይም አሁን እያገኘኙ በመሆኑ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።

እየተሰጠ ያለው ድጋፍ ሳይቆራረጥ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

በኃይለየሱስ ስዩምወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.