Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ5 አመት ስትራቴጂክ እቅድ ውይይት እየተደረገበት ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ5 አመት ስትራቴጂክ እቅድ ውይይት እየተደረገበት ነው።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት መአዛ አሸናፊ በተገኙበት ውይይት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንቶችም እየተሳተፉ ነው።
የህግ ባለሙያዎች የፍትህ አካላት እየተሳተፉበት በሚገኘው በዚሁ መድረክ÷ በ5 አመቱ የዳኝነት ስርአትና አገልግሎቱ የት መድረስ እንዳለበት የሚያመላክት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ ነው ውይይቱ ያተኮረው።
ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት መአዛ አሸናፊ÷ ከ2012 ጀምሮ የተቀመጡት ግቦች የዳኝነት ነጻነት፣ ገለልተኝነትን ማሻሸል፣ የዳኝነት ቅልጥፍናና ጥራት እንዲሁም ተደራሸነትን ማሳደግ ብሎም አስተዳደራዊ ድጋፎችን ማጠናከር መሆናቸውን ገልጸዋል።
ነጻ ፍርድ ቤቶችን መገንባት የሪፎርሙ ዋና ማጠንጠኛ መሆኑን ያነሱት ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ የአምስት አመቱ የፍርድ ቤቶቹ ራእይ የህዝብን አመኔታ ማግኘት ነው ብለዋል።
የዴሞክራሲ ሂደቱ ላይ በጎ ተፅእኖ የሚፈጥሩበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ያሉት ፕሬዚዳንቷ÷ ይህ እንዲሳካ ከፍተኛ ጥረትና ብስለት የተሞላበት አካሄድ ይጠይቃል ብለዋል።
ውይይቱ፣ ለስትራቴጂክ እቅዱ ገንቢ ይሆናሉ ተብለው የሚታመኑ ሃሳቦች እየተነሱ ነው።
በሀብታሙ ተ/ስላሴ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.