Fana: At a Speed of Life!

ከ650 በላይ ከስደት ተመላሽ ዜጎች በተለያዩ የሙያ መስኮች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ሲያሰለጥናቸው የነበሩ ከ650 በላይ ከስደት ተመላሽ ዜጎችን ዛሬ አስመርቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከከተማ አስተዳደሩ ቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ለአራተኛ ዙር ነው ከስደት ተመላሾችን አሰልጥኖ ያስመረቀው።
በምረቃት መርሃ ግብሩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥረር አባይን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች መሳተፋቸውን ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ሳይለያቸው በሀገር ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል ምሳሌ ይሆናሉ ብለዋል በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር ዓባይ፡፡
ዜጋ ተኮር ፖሊሲ የመንግስት ግልፅ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በመሆኑ በውጭ የሚኖሩ ዜጎቻችን ተገቢውን ክብር አንዲያገኙ እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት።
የዜጎች ሰብአዊ መብት እንዲከበር ከመስራት ባሻገር በአገር ውስጥ የስራ እድል በማስፋት ዜጎችን ተጠቃሚ የምያደርግ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.