Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በተለያዩ ሀገራት በመንቀሳቀስ የዲፕሎማሲ ስራ መስራቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በተለያዩ ሀገራት በመንቀሳቀስ የዲፕሎማሲ ስራ መስራቱን አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸው የዲፕሎማሲ ስራ እና ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በተለያዩ ሀገራት በመንቀሳቀስ በርካታ የዲፕሎማሲ ስራዎች እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታዎች እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላለፉ መልዕክቶችን ማድረሳቸውንም ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ልዑካኑ ከአውሮፖ ህብረት ጋር ምክክር ማካሄዳቸውንም አንስተዋል፡፡

በውይይቱ ወቅትም በተለይም ኢትዮጵያ ከአውሮፖ ህብረት ጋር ባላት ግንኙነት ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸውንም ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም በትግራይ ክልል ስላለው የእርዳታ ስርጭትና አሁናዊ ሁኔታ እንዲሁም ከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር ተያይዞም ተፈጽመዋል የተባሉ ጥሰቶችን ነፃና ገለልተኛ በሆነ መንገድ ምርመራ እንዲካሄድ ኢትዮጵያ በሯን ክፍት እንደምታደርግ ለአውሮፖ ህብረት ገለጻ መደረጉን አውስተዋል፡፡

ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲጋር በተያያዘም በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና አምባሳደሮች ጋር በርካታ ስራዎች መሰራታቸውንም ነው የተናገሩት፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ዜጎች ከተለያዩ የዓረብ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ መደረጉን እና በተለያዩ ዓለማት የሚገኙ የዳያስፖራ አባላት ለህዳሴው ግድብ ድጋፍ ስለማድረጋቸው አብራርተዋል፡፡

በዘቢብ ተክላይ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.