Fana: At a Speed of Life!

በሀዋሳ ከተማ አቀፍ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሀዋሳ ከተማ አቀፍ የብልፅግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ለፓርቲዉ ሲያካሄዱት የነበረዉን ድጋፍ ማጠቃለያዉን በተለያዩ ዝግጅቶች በመስቀል አደባባይ አካሂደዋል፡፡

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በመድረኩ በመገኘት እንደተናገሩት፥ ለሀገራችን የወደፊት ራዕይ እውን መሆን ምርጫ ብቸኛው አማራጭ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ከጀመረ ወዲህ ከፍተኛ ማህበራዊ እና ፓለቲካዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ስር ነቀል ሂደቶች መመልከት ችለናልም ብለዋል ከንቲባው፡፡

ለዚህ ለውጥ እውን መሆንም የብልፅግና ፓርቲ ትልቁን ድርሻ የተወጣ የህዝብ ፓርቲ እንደሆነም ነው ከንቲባው የገለጹት፡፡

በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫም የብልፅግና ፓርቲ ህዝባዊ ወገንተኝነቱን በተጨባጭ በማሳየት ብቁ ተፎካካሪ በመሆን ለህብረ ብሔራዊ ፌድራሊዝም እውን መሆን የበኩሉን ሚና ይወጣልም በማለት ከንቲባው ተናግረዋል፡፡

የሀዋሳ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ካሱ አሩሳ፥ ለኢትዮጵያ የለውጥ ዕድገት እውን መሆን የብልፅግና ፓርቲ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

በዚህ በዛሬው እለት በተጠናቀቀው የህዝብ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ብልፅግና ፓርቲን በመወከል ለክልል እና ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሚወዳደሩ እጩዎችን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች መገኘታቸዉን የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.