Fana: At a Speed of Life!

በአርሲ ዞን የተራቆቱ ተራሮችን ወደ ቀደመው ይዞታችው ለመመለስ እየተሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአርሲ ዞን የተራቆቱ ተራሮችን ወደ ቀደመው ይዞታችው ለመመለስ እየተሰራ እንደሚገኝ አርሲ ዩንቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

ዪንቨርሲቲው በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የጉመጉማ ተራራን ጥብቅ ደን ለማድረግ እየሰራው ነው ብሏል፡፡

የአካባቢው ማህበረሰብ በተራራው መራቆት መጎዳታቸውን የገለጹ ሲሆን፥ ከአሁን በኋላ ተራራውን ባለማረስ መንግስት በሚያመቻችላቸው መሠረት ለማልማት እንደሚጠቀሙም ነው የተናገሩት፡፡

ተራራው በመታረሱ እና የተፋሰስ ስራ ባለመሰራቱ ከስሩ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች በጎርፉ ተጎጂዎች እንደ ነበሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡

የተፋሰሶች ልማቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ገዛሁ፥ ከተራራው ላይ ታጥቦ የሚሄደው አፈር የደመበል ሀይቅን በደለል እንዲሞላና ሀይቁ ለእመቦጭ እንዲጋለጥ ሲያደረጉ መቆይታቸውን አንስተዋል፡፡

የተተከሉት ችግኞች በመንከባከብ ወደ ቀድሞው ይዞታው እንዲመለስ መስራት አለብንም ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፡፡

በኦሊያድ በዳኔ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.