Fana: At a Speed of Life!

ቀይ መስቀል በትግራይ ክልል ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉና ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አሰታውቋል።

በማህበሩ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቴድሮስ ሞላው ÷ በአካባቢው ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች የሰብዓዊና የማህበራዊ አገልግሎት ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።

በዞኑ እስካሁን ለ5 ሺህ 600 ተፈናቃይ አባወራዎች የምግብ ማብሰያና የንጽሀና መጠበቂያ ቁሳቁስ እንዲሁም አልጋና ብርድልብስ ድጋፍ መደረጉን አንስተዋል።

በመጠለያ ጣቢያዎች አስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው 120 ነፍሰጡር እናቶች በነፍስ ወከፍ የ1 ሺህ ብር ድጋፍ መደረጉን ነው የገለጹት።

በዞኑ በአስገደት ጸንበላ ወረዳ በእንዳባጉና ከተማ ለችግር ለተጋለጡ 850 ወገኖች 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ መደረጉን ለአብነት ጠቅሰዋል።

ማህበሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በመድሀኒትና በውሃ አቅርቦት እንዲሁም አካባቢ ንጽህና ጨምሮ በበሽታ መከላከል ስራዎች በመሳተፍ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

በዞኑ ካለው የተፈናቃይ ቁጥር አንጻር እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተመጣጣኝ አለመሆኑን የጠቆሙት ሃላፊው ÷ ድጋፉን ተደራሽ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.