Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ ለ148 የግል ዕጩዎች የ50 ሺህ ብር ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ148 የግል ዕጩዎች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ለምርጫ ዕለት ወጪያቸው ማካካሻ ገንዘብ እንዲሰጥ ወስኗል።

የምርጫ ቦርድ የኮሚዩኒኬሽን አማካሪ ሶሊያ ሽመልስ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፥ በመግለጫቸውም ለፌዴራልና ክልል ምክር ቤት 148 የግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለእያንዳንዳቸው 50 ሺህ ብር ድጋፍ ለማድረግ ተነግሯል።

ቦርዱ ሰኞ ድምፅ የሚሰጥባቸውና የተወዳዳሪዎች ማንነት በቦርዱ ድረ ገፅ ላይ ይፋ ማድረጉንም ተናግረዋል።

“ከነገ ጀምሮ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይቻልም፤ ሚዲያዎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅስቀሳና የፓርቲዎች ፕሮግራም ማስተዋወቅ አይፈቀድላቸውም” ብለዋል።

ነገር ግን በቀጣይ ቀናት ስለመራጩ ህዝብ፣ ምርጫ ካርድ፣ ድምፅ አሰጣጥ፣ ድምፅ መስጫ ወረቀቶችን ለመራጮች ግልፅ በማድረግ ረገድ ዘገባዎች ቢሰሩ ይበረታታሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከምርጫ ጋር በተያያዘ ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል ከፌስቡክ ጋር በጋር እየሰራን ነው ያሉት አማካሪዋ፥ በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎችን እውነተኛነት ማረጋገጫና ሃሰተኛ መረጃዎችን ማስወረድ ላይ እንሰራለን ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.