Fana: At a Speed of Life!

ባይደን እና ፑቲን በጦር መሳሪያ ቁጥጥር እና በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ውይይት ለመጀመር ተስማምተዋል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና የሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን በጦር መሳሪያ ቁጥጥር እና በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ውይይት ለመጀመር ተስማምተዋል፡፡

የሁለቱ ሃያላን ሀገራት መሪዎች በትናንትናው ዕለት በጄኔቫ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሳይበር ደህንነት፣ በጦር መሳሪያ ቁጥጥር፣ በሩሲያው ተቃዋሚ አሌክሲ ናቫልኒ ዕጣ ፈንታ እና በቀጣይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው ዙሪያ በትኩረት መክረዋል፡፡

በዚህም ሁለቱ መሪዎች በሳይበር ደህንነት እና በጦር መሳሪያ ቁጥጥር ዙሪያ በቀጣይ ውይይቶችን ለመጀመር ስምምነት ላይ መድርሳቸው ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ ባለፈም ከ2020ው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ውዝግብ ምክንያት ከሁለቱም ሀገራት ወጠው የነበሩት አምባሳደሮች እንዲመለሱ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ ባይደን እና ፑቲን እስር ላይ በሚገኘው የሩሲያ ተቃዋሚ አሌክሲ ናቫልኒ ጉዳይ ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረስ አለመቻላቸው በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን ተቃዋሚው አሌክሲ ናቫልኒ በእስር ቆይታው ላይ ህይወቱን የሚያሳጣ አንዳች ነገር ቢከሰት ውጤቱ ለሞስኮ አስከፊ እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል፡፡
ምንጭ÷ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.