Fana: At a Speed of Life!

“የክፋት በርን ዘግተን የፍቅር በርን ከፍተናል” በሚል መሪ ሃሳብ የእርቀ ሰላም ስነስርዓት በአጣዬ ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)”የክፋት በርን ዘግተን የፍቅር በርን ከፍተናል” በሚል መሪ ሃሳብ የእርቀ ሰላም ስነስርዓት በአጣዬ ከተማ ተካሂዷል፡፡

የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አገኘሁ መክቴ እንደገለጹት፥ ይህ እርቅ ህብረተሰቡ ከስጋት ነጻ ሆኖ እንዲኖርና ወደ ልማት እንዲዞር ይረዳል።

እርቁ ቀደም ሲል እንደነበረው በሰላም ገበያ ወጥቶ ለመመለስ አስተዋጽኦ ጉልህ መሆኑን ጠቅሰው፥ ማህበራዊ መስተጋብርን ለማጠናከርና አንድ ሆኖ የሀገር ልማትን ለማረጋገጥ ጥሩ አጋጣሚ ነውም ብለዋል።

እርቁ ጥላቻን በማስወገድ ፍቅር የሚመሰረትበት ነው ያሉት ከንቲባው፥ ሁለቱ የአማራና የኦሮሞ ብሄሮች አንድ ከሆኑ የጥፋት ሀይሎችን ነጥሎ ለማውጣትና ለህግ ለማቅረብ እንደሚረዳም ገልጸዋል።

በእርቅ ስነስርዓቱ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች እና የአካባቢው የኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሌተናል ጀኔራል ደስታ አቢቼ በተገኙበት የሰንጋ ልውውጥ ማድረጋቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች በጋራ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ያካሄዱ ሲሆን ፥ የአረንጓዴ አሻራው የሰላም፣ የእርቅና የአብሮነት ምሳሌ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በኤፍራታና ግድም ወረዳ እንዲሁም በሸዋሮቢት ከተማ የእርቀ ሰላም ስነስርዓት መካሄዱ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.