Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የ6 ኛውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የ6 ኛውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ፡፡
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ለኢትዮጰያ ህዝብ ባስተላለፈው መልዕክት፥ ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ብሏል፡፡
የምርጫው ሂደት ተጀምሮ እሁን ያለበት ደረጃ እስኪደረስ በጨዋነትና በትዕግስት ላደረጋችሁት ድጋፍ እና ትብብር የላቀ ምስጋናውን እያቀረበ፤በቀሪው የምርጫ ሂደትም መርጫውን የሚያደናቅፍ አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ እነደተለመደው ሁሉ መረጃ በመስጠትና አስፈላጊውን ድጋፍ ለፀጥታ እና ደህንነት ኃይሉ በማድረግ የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
በተጨማሪም ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባስተላለፈው ምልዕክቱ፥ የምርጫ ህጉንና የስነ ምግባር ደንቡን አክብራችሁ እስከ አሁን ለምርጫው ሰላማዊነት የበኩላችሁን ገንቢ አስዋጾ በማበርከታችሁ ኮምሽኑ ምስጋናውን እያቀረበ፣ በቀጣይም በሚኖረው የምርጫ ሂደት እስከመጨረሻው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሀገራዊ ኃላፈነታችሁን እንድትወጡ ኮምሽኑ አጥብቆ ይጠይቃል ነው ያለው፡፡
መግለጫው ለፌደራልና የክልል የጸጥታና ደህንነት አካላትም መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን፥ መሰዋትነት በመክፈል ጭምር ፍጹም ገለልተኛ ሆናችሁ ሌት ተቀን እያበረከታችሁት ላላችሁት አስዋጾ ኮሚሽኑ ከልብ ማመሰገኑን በመግለጽ በቀጣይ ለሚኖር የድምጽ አሰጣጥና አጠቃላይ ለምርጫው ሂደት ስኬታማነት የተሰጣችሁን ሰላም ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነታችሁን ልክ እደቀደመው ጊዜ ሁሉ እንድትወጡ ከአደራ ጭምር አሳስቧል፡፡
ኮሚሽኑ ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትገኝበትን ወሳኝ ምዕራፍ ከግመት ውስጥ በማስገባት የምርጫ ሂደቶች ከሁከትና ብጥብጥ የፀዱ እንዲሆኑ ከፀጥታና ደህንነት መዋቀር ጋር የተቀናጀ የምርጫ ደህንነት እቅድ በማዘጋጀት በቅድመ ምርጫ፣በምርጫ ዕለት፣ በድህረ -ምርጫ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ውስጣዊ እና ውጫዊ የፀጥታ ሁኔታዎችን በአግባቡ በመተንተን እና በመለየት አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ሲሰራ ቆይቷል፡፡
ከዚህ አንጻር 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ማጠናቀቅ ለሀገራችን ሰላም መረጋጋት እንዲሁም የሀገራችንን ታላቅነት ለመላው አለም የምናሳይበት ታላቅ ኩነት መሆኑን ለገጽታችን ግንባታ ያለውን ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን የተረዳው ኮሚሽኑ የውስጥና የውጭ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ፀጥታውን ለማናጋት፣የምርጫውን ሰላማዊነት ለማደፍረስና የሁከትና ብጥብጥ መንስኤ ለማድረግ እንደሚንቀሳቀሱ ከወዲሁ በመረዳት ምንም አይነት ህገ-ወጥ እንቀስቃሴ በየትኛውም አከባቢ እንዳይኖር ከፌደራል እሰከ ክልል ያሉ የሀገራችን የጸፀጥታና ደህንነት መዋቅሮች በከፍተኛ ኃላፊነትና ተጠያቂነት የተሰጣቸውን ሀገራዊ ተልዕኮ በብቃት መወጣት የሚያስችላቸው ሁለንተናዊ አቅም በመገንባት ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስምሪት ግብቷል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለህዝቡ እና ለስራችን ከፍተኛ እገዛ የሚያደርጉት አስፈላጊ እና ወሳኝ የሆኑት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች መምርጫ ወቅት ያለ በቂ ምክንያት እንዳይቋረጡ የሚመለከታቸው አካላት ኃላፊነታችውን በአግባቡ እንዲወጡ ኮሚሽኑ በአንክሮ ያሳስባል፡፡
በመጨረሻም መላው የሀገራችን ህዝብ እና የፀጥታ ሀይል ከመቼውም ጊዜ በላይ በመቀናጀት ይህንን ታሪካዊ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እንድንወጣ ጥሪያችንን በከፍተኛ አክብሮት እያቀርብን፣ በድምጽ መስጫ ዕለትና በድህረ-ምርጫ ወቅት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሁሉ በህግ አግባብ ብቻ እንዲሆኑ ኮሚሽኑ በጥቅ ያሳውቃል፡፡
ኮሚሽኑ በድጋሜ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም አደራሳችሁ ሲል በማለት መልካም ምኞቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስተላለፈ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.