Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ጎንደር ዞን ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጪው ሰኞ ለሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን የደቡብ ጎንደር ዞን ምርጫ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት አስታወቀ።

የፅ/ቤቱ ሀላፊ አቶ አምሳሉ በለጠ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት በዞኑ ዘጠኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚወዳደሩ ሲሆን እነዚህም 301 እጩዎችን አስመዝግበዋል።

የምርጫ ሂደቱን በ19 የምርጫ ክልሎች 1ሺህ 472 የምርጫ ጣቢያዎችን በማዘጋጀት ለመከወን እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን የገለፁት አቶ አምሳሉ የምርጫ ማስፈፀሚያ ቁሳቁስ ስርጭትም እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

በዞኑ የፎገራ 1 ምርጫ ክልል አስተባባሪው አቶ ሀይሉ ባየ እንዳሉት የምርጫ ቁሳቁስን በአካባቢው በተዘጋጁ 86 የምርጫ ጣቢያዎች ለማዳረስ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

የከምከም 1 ምርጫ ክልል አስተባባሪዋ ወ/ሪት ቤተልሔም ሰጡ በበኩላቸው ለ74 የምርጫ ጣቢያዎች የሚሆኑ ግብአቶችን ደህንነታቸው በተጠበቀ መንገድ እያጓጓዙ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የዞኑ ነዋሪ የሆኑና አስተያየታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሰጡ ግለሰቦችም ሰኞ ለሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ድምፃቸውን በመስጠት የዜግነት ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።

በደቡብ ጎንደር ዞን በምርጫው እለት 950ሺህ የሚሆን ህዝብ ድምፁን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በሙሉጌታ ደሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.