Fana: At a Speed of Life!

ትስስር ለሕዳሴ ግድብ ጥምረት ተመሰረተ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በቅንጅት የሚሰራ “ትስስር ለሕዳሴ ግድብ” የተሰኘ ጥምረት በይፋ ተመሰረተ።

ጥምረቱ ስለ ዓባይ ግድብ ያለውን እውነታ ለዓለም ማህበረሰብ ለማስረዳት የሚሰራ ሲሆን በሃገር ውስጥና በውጭ ያሉ ምሁራንና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሚናቸውን የሚወጡበት መሆኑን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ተናግረዋል።


የሙያ ማህበራት፣ የሃይማኖት ተቋማትና የፖለቲካ ፓርቲዎች አባሎቻቸውንና ተከታዮቻቸውን በማስተባበር ለሕዳሴ ግድቡ ድምጽ እንዲሆኑ አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችሉበት እንደሆነም አክለዋል።

ኢትዮጵያውያንን በአንድ አጀንዳ የሚያሰባስበው ጥምረቱ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ የሚያስችላቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

“አባቶች መስዋዕትነት ከፍለው ሃገሪቷን አስረክበውናል” ያሉት ዶክተር አረጋዊ፤ “እኛም ለቀጣዩ ትውልድ ግድቡን አጠናቀን በማስተላለፍ ታሪክ ማኖር አለብን” ብለዋል።

ጥምረቱ 12 አባላት ያሉት አስተባባሪ ኮሚቴ ያለው ሲሆን ሃብት አሰባሰብ፣ አካባቢ ጥበቃ፣ ህዝባዊ ዲፕሎማሲ እንዲሁም መገናኛ ብዙሃንና ተግባቦትን ያካተተ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.