Fana: At a Speed of Life!

በምርጫው መሳተፍና ሠላምን መጠበቅ የዜግነት ግዴታ ነው – የቦዲቲ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምርጫው ላይ መሳተፍና ሠላምን መጠበቅ የዜግነት ግዴታችን ነው ሲሉ በወላይታ ዞን የቦዲቲ ከተማና በዳሞት ፑላሳ ወረዳ የሻንቶ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

ቀጣዩን ጊዜ ለመወሰን ካርዳቸውን ይዘው የምርጫውን ቀን እየተጠባበቁ መሆኑንም ገልፀዋል ።

ነዋሪዎቹ ምርጫ ነገን የተሻለ ለማድረግ በህግ የተደነገገ የዜግነት መብት መሆኑን በመገንዘብ በሀገረ መንግስት ግንባታው ድምፅ በመስጠት ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን አንስተዋል ።

ይሆነኛል ይበጀኛል ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የሀገራቸውን የነገ እጣ ፋንታ ለመወሰን በምርጫ መሳተፍ ከዜጎች የሚጠበቅ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ በአንድ ሀገር የዴሞክራሲ መጎልበት ምርጫ ትልቅ ድርሻ አለው ብለዋል።

የወሰዱትን ካርድ ትርጉም ባለው መልኩ ለመጠቀምና ምርጫውን ለማካሄድ የሠላም ጉዳይ ወሳኝ በመሆኑ ለሰላማዊነቱ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም ጠይቀዋል፡፡

ሰላም የሁሉም ነገር ቁልፍ ነገር መሆኑን በመጠቆም ፍትሐዊ ፣ ተአማኒ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡም ነው የገለጹት፡፡

በማስተዋል አሰፋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.