Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት መካሄድ መጀመሩን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሙዩኒኬሽን ሃላፊ ሶልያና ሽመልስ በክልሎች የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተካሄደ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በሂደቱም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድጋፍ ማድረጉንም ገልጸዋል።

ከደቡብ ምእራብ ህዝበ ውሳኔ ጋር በተያያዘ ሰኔ 14 ቀን ምርጫውን ለማካሄድ የተካሄደው ምዝገባ ጳጉሜን 1 ቀን 2013 ዓ.ም በሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ጥቅም ላይ ይውላል ብለዋል።

ይህም ድጋሚ ምዝገባ ሳይካሄድ ለምርጫው በተካሄደው ምዝገባ ህዝበ ውሳኔው ይካሄዳልም ነው ያሉት፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም መራጮች ከመረጡ በኋላ ካርዳቸውን ሳይመልሱ ማህተም ተደርጎ በድጋሚ እንዲጠቀሙባቸው እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

እስካሁን ከ120 በላይ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች መግባታቸውን ጠቅሰው፥ በቀጣይም ፈቃድ ወስደው ወደ ሀገር የሚገቡ ታዛቢዎች እንደሚኖሩም አስረድተዋል።

ካርድ የጠፋባቸው ዜጎች መመዝገባቸው ተረጋግጦና ቃለጉባኤ ተይዞ መምረጥ እንደሚችሉም ነው የተናገሩት።

የፓርቲ ወኪሎች ምዝገባና ባጅ የመውሰጃ ጊዜ እስከ እሁድ ማታ መራዘሙንም ነው የገለጹት።

የድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የተወካዮች ምክር ቤት 1 መሆኑንና የክልል ምክርቤት ተወካዮች ቁጥር ግን እንደየ ምርጫ ክልሉ እንደሚለያይ መራጮች መገንዘብ አለባቸውም ብለዋል ሃላፊዋ።

ከቦርዱ እውቅና ውጭ በተከፈቱ የምርጫ ጣቢያዎች ለመራጮች መብት ሲባል እንደ አዲስ ምዝገባ እየተካሄደ በምርጫ ጣቢያዎቹ የሚመርጡ ሲሆን፥ ሲመጡ ግን የተመዘገቡቡትን ካርድ በመያዝ እንደሚመሳከር አንስተዋል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.