Fana: At a Speed of Life!

ጤና ሚኒስቴር በምርጫው የሚሳተፉ ዜጎች ከኮቪድ19 እንዲጠነቀቁ አሳሰበ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጤና ሚኒስቴር በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚሳተፉ ዜጎች ከኮቪድ19 እንዲጠነቀቁ አሳሰበ።

ሀገር አቀፍ ምርጫው የኮቪድ19 ወረርሽኝ በዓለም አቀፍ እና በኢትዮጵያም እየተስፋፋ ባለበት ወቅት ላይ የሚካሄድ ምርጫ መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ፣ ሁሉም ዜጋ በምርጫ ዕለት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል ብሏል።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ኮቪድ-19ን አስመልክቶ በምርጫው ዕለት ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎችን ይፋ አድርጓል።

ዜጎች በዕለቱ ወደ ምርጫ ጣቢያ ሲሄዱ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ /ማስክ መጠቀም፣ ከማንም ጋር መጨባበጥም ሆነ በመተቃቀፍ ሰላምታ አለመለዋወጥ፣ ሰልፍ ላይ ወይም ማብራሪያ በሚሰጥ ጊዜ ከሌላው መራጭ ቢያንስ አንድ ሜትር ያህል ርቀትን መጠበቅ፣ እንዲሁም ንፁህ ውኃ ወይም ሳኒታይዘር በመጠቀም፣ የእጅ ንጽህናን መጠበቅ እንዳለባቸው አስገንዝቧል።

ለዚሁ ሥራ በየምርጫ ጣቢያው የተሰማሩ የጤና ኤክሰቴንሽን ሠራተኞች እና ባለሙያዎች ሁሉም ዜጋ ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጎ ምርጫውን ማከናወን እንዲችል ሙያዊ እገዛ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርቧል።

ህብረተሰቡም ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክር ተግባራዊ እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.