Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን የኮሮና ቫይረስ ክትባት ወደ ታይዋን ልካለች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2013 ፣ (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን የኮቪድ-19 ክትባቶችን ወደ ታይዋን መላኳ ተሰምቷል፡፡

አሁን ላይ ወደ ታይዋን የተላከው የክትባት መጠንም ከዚህ በፊት ከታቀደው በሶስት እጥፍ የሚልቅ መሆኑን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ይህም አሜሪካ በጤናው ዘርፍ ከታይዋን ጋር ያላትን ግንኙነት ከማሳደጉ ባለፈ በሀገሪቱ የሚስተዋለውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መቆጣጠር ያስችላል ነው የተባለው፡፡

የታይዋን ፕሬዚዳንት ትሳይ ኢንግ ዌን በበኩላቸው ÷ አሜሪካ በዚህ የችግር ወቅት ፈጥና በመድረስ ላደረገችው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ድጋፉ ለቀጣይ የሁለትዮሽ ግንኙነት የመሰረት ድንጋይ የሚጥል መሆኑንም ነው ፕሬዚዳንቷ የገለጹት፡፡

በአንፃሩ ቻይና አሜሪካ በክትባት ዲፕሎማሲ ሰበብ በታይዋን ላይ የምታካሂደውን አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት እንድታቆም እያሳሰበች ነው፡፡

ምንጭ ÷ አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.