Fana: At a Speed of Life!

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የምርጫ ቁሳቁስ እየተሰራጨ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2013 ፣ (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ነገ ለሚካሄደው ምርጫ ቁሳቁስ እየተሰራጨ ይገኛል።

በክፍለ ከተማው በነገው ዕለት ከ 135 ሺህ በላይ መራጮች ድምፃቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በክፍለከተማው በሁለት የምርጫ ክልል በ121 የምርጫ ጣቢያዎች ለምርጫው አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች አየተሰራጩ እንደሚገኙ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባደረገው ቅኝት ለመመልከት ችሏል።

ተጨማሪ የቁሳቁስ ስርጭቱ እሰከ ዛሬ 9:00 ይጠናቀቃልም ነው የተባለው።

በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከ 300ሺህ በላይ ችግኞች ከምርጫው ጎን ለጎን እንደሚተከሉ የተገለጸ ሲሆን፥ ለችግኝ መትከያ የሚሆን ቦታ መዘጋጀቱም ነው የተነገረው።

በምንይችል አዘዘው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.