Fana: At a Speed of Life!

በጌዴኦ ዞን ለቅድመ ምርጫ የሚደረጉ ዝግጅቶች ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2013 ፣ (ኤፍ ቢ ሲ) ለ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚደረጉ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የጌዴኦ ዞን ምርጫ ማሰተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በዞኑ 7 የምርጫ ክልሎች እና 600 ምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን የማስተባበሪያው ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ አበባየሁ ገልፀዋል፡፡

በዞኑ ሶስት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለውድድር መቅረባቸውን ነው አስተባባሪው የተናገሩት፡፡

እነዚህ ፓርቲዎች እያንዳንዳቸው አንድ አንድ የሕዝብ ተወካዮች እና ሶስት ሶስት የክልል ተወካዮችን በእጩነት አስመዝግበዋል ነው ያሉት፡፡

በነገው ዕለት ለሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችንም የማሰራጨት ሥራም እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በአጠቃላይ በዞኑ 470 ሺህ ዜጎች ድምጽ መስጠት የሚያስችለውን የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውም ተመላክቷል፡፡

በታሪክነሽ ሴታ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.