Fana: At a Speed of Life!

በባህርዳር የምርጫ ክልል በሚገኙ የምርጫ ጣቢዎች የምርጫ ቁሳቁስ እየተሰራጨ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በባህርዳር ከተማ የምርጫ ክልል በሚገኙ የምርጫ ጣቢዎች የምርጫ ቁሳቁስ እየተሰራጨ ይገኛል።

በአፄ ቴወድሮስ ከፍለከተማ 25 የምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን፥ በጠይማ ምርጫ ጣቢያ የምርጫ ቁሳቁስ መድረሱን ፋና ብሮድካስቲንግ በስፍራው ቅኝት አድርጓል።

የባህር ዳር ምርጫ ክልል አስተባባሪ ወይዘሮ ማህደር አዳሙ ለጣቢያችን እንደገለጹት፥ ዘጠኝ የፓለቲካ ፓርቲዎች ዕጩ ያቀረቡ ሲሆን፥ አንድ የግል ተወዳዳሪ አለ ብለዋል።

በ144 የምርጫ ጣቢያዎች አስፈላጊ የምርጫ ቁሳቁሶች እየተሰራጩ መሆኑን የገለጹት ሀላፊዋ፥ ስርጭቱ በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል ብለዋል።

በድምፅ መስጫው ቀን መራጩ እራሱን ከኮሮና ቫይረስ መከላከል እንዲችል የመከላከያ ግብዓቶች እየቀረቡ መሆኑንም ገልጸዋል።

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.