Fana: At a Speed of Life!

በአጋሮ ከተማ ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚደረገው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2013 ፣ (ኤፍ ቢ ሲ) በጂማ ዞን አጋሮ ከተማ ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን በከተማዋ የምርጫ ቦርድ አስተባባሪ አስታውቋል፡፡

በአጋሮ ከተማ በጎማ 2 የምርጫ ክልል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የኢዜማና የእናት ፓርቲ አባላት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት ይወዳደራሉ።

በምርጫ ክልሉ 85 የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን÷ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የጎማ ሁለት ምረጫ ክልል አስተባባሪ አቶ ረሻድ አብዱልቃድር ተናግረዋል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በአንዳድ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ባደረገው ቅኝትም÷ የሚስጥራዊ ድምፅ መስጫ ቦታዎች መዘጋጀታቸውንና ሌሎች ለምርጫ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች እየቀረቡ መሆኑን ተመልክቷል።

የአጋሮ ከተማ ነዋሪዎችም ምርጫው በሚካሄድበት በነገው ዕለት ጠዋት ከ12፡00 ጀምሮ በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምፃቸውን ይበጀናል ለሚሉት ፓርቲ እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

የከተማዋ ወጣቶች በበኩላቸው ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፀጥታ አስከባሪ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

በሙክታር ጠሃ እና አፈወርቅ አለሙ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.