Fana: At a Speed of Life!

ምርጫው ያለምንም የጸጥታ ችግር ለማከናወን የተቀናጀ የጸጥታ መዋቅር በስራ ላይ ነው- የከፋ ዞን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ምርጫው ያለምንም የጸጥታ ችግር ለማከናወን የተቀናጀ የጸጥታ መዋቅር በስራ ላይ መሆኑን የከፋ ዞን አስታወቀ፡፡
የዞኑ የሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ ሃብታሙ አለሙ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት ÷ነገ የሚደረገውን ሃገር አቀፍ ምርጫ የከፋ ዞን ያለጸጥታ ችግር ለማከናወን ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል ።
ዝግጅቱ የቅድመ መርጫን ፣የምርጫውን ጊዜና ድህረ ምርጫው ታሳቢ ያደረገና በሶስት ምዕራፎች የተጠናቀረ ነው ተብለዋል ።
በዞኑ በሚገኙ 7 የምርጫ ክልሎች 6 መደበኛ እና 1 ልዩ የምርጫ ክልል ፣ 461 የምርጫ ጣቢያዎች መኖሩን ገልፀው በእነዚህ ጣቢያዎች የጸጥታ መዋቅሩ ሙሉ ዝግጅት ማደረጉንና በቦታዎቹ መገኘታቸውን ገለጸዋል።
ዞኑ የምርጫውን ሂደት ያለምንም ችግር እንዲጠናቀቅ ከማህበረሰቡ ጋር ከሚሰራቸው ስራዎች በተጨማሪ ከክልሉና ከዞን ከተዘጋጁ የጸጥታ አካላት በተጨማሪ 50 የሚሆኑ እና በ5 የተከፈሉ ፓትሮል ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
በዞኑ እስካሁን ምንም ዓይነት የጸጥታ ችግር እንዳልገጠማቸው ገልፀው ይህ የተቀናጀ የጸጥታ ማስጠበቅ መዋቅር በድህረ ምርጫውም የሚቀጥል ነው ብለዋል።
በፍሬህወት ሰፊው
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.