Fana: At a Speed of Life!

በአውሮፓ ዋንጫ በምድብ 1 ዌልስ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ በምድብ 1 ዌልስ ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን አረጋግጣለች፡፡

ትናንት ምሽት ከጣሊያን ጋር የተጫወቱት ዌልሶች 1 ለ 0 ቢሸነፉም ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ጣሊያን ጨዋታውን ፔሲና ባስቆጠራት ጎል 1 ለ 0 አሸንፋለች፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ጣሊያን ምድቡን 9 ነጥብ በመያዝ ስትጨርስ ዌልስ በ4 ነጥብ በአንድ ንጹህ ጎል ሁለተኛ በመሆን ጥሎ ማለፉን ተቀላቅላለች፡፡

በሌላኛው የምድቡ ጨዋታ ስዊዘርላንድ በሴፈሮቪች እና ሻኪሪ ጎሎች ቱርክን 3 ለ 1 አሸንፋ ተመሳሳይ አራጥ ነጥብ በመያዝ አጠናቃለች፡፡

ዌልስ ተጨማሪ አንድ ጎል ሲኖራት ስዊዘርላንድ አንድ የግብ እዳ በመያዝ የጥሎ ማለፍ ተሳትፎዋን ለማረጋገጥ የሌሎች ምድብ ጨዋታዎችን መጠናቀቅ ትጠብቃለች፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.