አንዲት እናት ድምጽ ከሰጡ በኋላ ወንድ ልጅ በሰላም ተገላገሉ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ አንዲት እናት ድምፅ ለመስጠት በሄዱበት የጀመራቸው ምጥ ድምጽ ከሰጡ በኋላ በሰላም ተገላገሉ፡፡
አበራሽ ጉታ የተባሉት መራጭ ድምፅ ለመስጠት በሄዱበት ሄጦሳ ዙሪያ ምርጫ ጣቢያ ምጥ ጀመራቸው፡፡
እንደምንም ድምፅ ከሰጡ በኋላ ወደ ህክምና ተቋሞ በማቅናት ወንድ ልጅ ተገላግለዋል፡፡
ለልጃቸውም ታሪኩ የሚል ስያሜ ሰጥተዋል ሲል የሄጦሳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል፡፡
በኤርሚያስ ቦጋለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!