Fana: At a Speed of Life!

ከማንኛውም ጣልቃ ገብነት ነፃ በሆነ መልኩ መምረጣቸውን የአራዳ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከማንኛውም ሰው ጣልቃ ገብነት ነፃ በሆነ መልኩ ድምፅ መስጠታቸውን በአራዳ ክፍለ ከተማ የምርጫ ክልል 1/9 ባሉ የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ የሰጡ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በክፍለ ከተማው በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ቅኝት ባደረገበት ወቅት ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት ÷ከጣቢያው መግቢያ ጀምሮ ስለ ምርጫው ሂደት ተመሳሳይ የሆነ ግንዛቤ እንዲኖራቸው መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ያለማንም ተፅዕኖም ይሆነኛል፤ ይመራኛል ፤ላሉት ፖርቲ ድምፅ መስጠታቸውንም ገልፀዋል።

የድምፅ መስጫ ሂደቱ ተጠናቆ ውጤት ሲገለፅም ሰላማዊ በሆነ መልኩ አሸናፊ በሆነው አካል ለመተዳደር ዝግጁ መሆናቸውን ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

በትዝታ ደሳለኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.