Fana: At a Speed of Life!

ሴት ልጅ የተገላገለችው የምርጫ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ባለቤት ድምጽ ሰጠች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሊት የድምፅ መስጫ ሰዓቱ ሲቃረብ የተገላገለችው እመጫት የልጇን ስያሜም “ምርጫዬነሽ” የሚል መጠሪያ ሰጥታታለች፡፡
ወይዘሮ አለምነሽ ዘርጋዉ ትባላለች በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ የቅበት ከተማ ነዋሪ ነች ።
በ6ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ ካርድ አውጥታ የምርጫዉን ቀን ስትጠባበቅ ቆይታለች።
ዛሬ ሌሊት ግን ለእርሷ የአብራኳን ክፋይ ለማየት የተለየ ቀን ሆኖ አገኘችው።
ወትሮም ቢሆን በዚህ ታሪካዊ ቀን ድምጽ ለመስጠት ምኞቷ ነበርና ገና ያልጠነከረዉ የአራስ ወገቧ የህመም ስሜት ሳይበግራት በሰዎች እገዛ ወደ ቅበት 01/ምርጫ ጣቢያ በማቅናት በሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ላይ የራሷን አሻራ አሳረፈች።
የሴት ልጇን ስያሜም ምርጫዬነሽ ስትል ሰየመቻት።
እንደ ወይዘሮ አለምነሽ ገለጻ ምን ግዜም ምርጫ በመጣ ቁጥር ከልጄ ልደት ለይቼ አላየዉም ስትል ጠቁማለች።
ባለቤቷ ብሩክ ሀብታሙ የስልጤ ዞን ምርጫ ቦርድ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ነው።
እርሱ በተሰጠዉ ድርብ ድርብርብ ሀላፊነት ላይ ሆኖ የባለቤቱን መገላገል የሰማዉ በስራ ገበታዉ ላይ ሆኖ ነዉ።
በዚህ ታላቅ ሀገራዊ ሁነት ላይ ሆኖ ይህንን ታላቅ የደስታ ዜና መስማቱ እንዳስደሰተዉ ተናግሯል።
በሶዶ ለማ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.