Fana: At a Speed of Life!

የምርጫው የእስካሁን ሂደት በመልካም ሁኔታ እየተከናወነ ነው – የአፍሪካ ኅብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድን

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምርጫው የእስካሁን ሂደት በመልካም ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን የአፍሪካ ኅብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪና የናይጄሪያ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ገለጹ።

የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ዛሬ ረፋዱ ላይ በአዲስ አበባ ምርጫ ክልል 21/22 ምርጫ ጣቢያ 4 እና 5 የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በአካል ተገኝቶ ታዝቧል።

የቡድኑ መሪ የሆኑት ኦባሳንጆ “ቡድኑ ከገባበት ቀን ጀምሮ የምርጫ ሂደቱን በተለያየ መልኩ ሲከታተል ነበር” ብለዋል።

የምርጫ ዝግጅቱን በተመለከተ የአፍሪካ ኅብረትን ጨምሮ ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተገናኝተው ሠፋ ያለ ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ከጸጥታ ተቋማት፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎችና ከሌሎች አካላት ጋር የምርጫውን ዝግጅት በተመለከተ መወያየታቸውንም አስታውሰዋል።

የኮሮናቫይረስ ወረርሺኝ፣ የጸጥታና የሎጅስቲክስ ችግሮች ቢስተዋሉም የምርጫ አስፈጻሚ አካላት ይህንን ተቋቁመው ምርጫውን ማስፈጸማቸውን ጠቁመዋል።

የምርጫው የእስካሁን ሂደትና የዛሬ ድምጽ አሰጣጥ በመልካም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የቡድኑ መሪ ገልጸዋል።

ቡድኑ አዲስ አበባን ጨምሮ በአንዳንድ የክልል የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ሂደቱን በተመለከተ ተዘዋውሮ መመልከቱን ጠቁመው “የእስስካሁኑ ሂደት ጥሩ ደረጃ ላይ ነው” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

መራጩ ህዝብ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በአግባቡ በመረዳትና በመተግበር ምርጫ ቅደም ተከተላዊ ሥነ-ሥርዓቱን በተከተለ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።

በምርጫው ተሳታፊ የሆኑ ከተለያዩ የፓርቲ አባላቶችን ማነጋገራቸው ገልጸው፤ እስካሁን ቅሬታ ያቀረበ ፓርቲ አለመኖሩን አረጋግጠዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.