Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል፣በወላይታ ዞንና በጅማ ከተማ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን ምርጫ በተካሄደባቸው የምርጫ ክልሎችና ጣቢያዎች ድምፅ የመስጠት ሂደቱ ተጠናቋል ።
በሰባት የምርጫ ክልሎች በ560 የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ የተሰጠ ሲሆን በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ህብረተሰቡ ከማለዳው 12 ሰአት ጀምሮ ድምፁን ሲሰጥ ውሏል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ቅኝት ባደረገባቸው የምርጫ ክልሎችና የምርጫ ጣቢያዎች ድምፃቸውን የሰጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንደነበር ገልፀው ከዚህ ቀደም ከነበሩ ምርጫዎች የተሻለ ዴሞክራሲ የሰፈነበት እንደነበር ተናግረዋል ።
ምርጫ ቦርድ ውጤቱን እስከሚያሳውቅ ድረስም ሁሉም በትዕግስት መጠባበቅ አለበት ብለዋል፡፡
እንዲሁም በምርጫው የተሳተፉ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የህዝብ ድምፅ ማክበር አለባቸው ነው ያሉት።
በተያያዘ በአፋር ክልል ድምፅ የመስጠት ሂደቱ ተጠናቋል፡፡
በክልሉ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ ተጠናቆም ቆጠራ ተጀምሯል ።
እንዲሁም በጅማ ዞን 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሠላም ተጠናቋል፡፡
በዞኑ በ18 የምርጫ ክልል ስር ባሉ 1 ሺህ 583 የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫው በሠላም ሲካሄድ ውሏል።
በማስተዋል አሰፋ፣ በርስቴ ፀጋዬና በሙክታር ጠሃ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.