Fana: At a Speed of Life!

መገናኛ ብዙሃን ሙያዊ ስነ-ምግባርን ባከበረ ስሜት ለሰሩት ዘገባ ምስጋና ይገባቸዋል – የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መገናኛ ብዙሃን የምርጫውን ሂደት ሙያዊ ስነ-ምግባርን ባከበረና ከፍ ባለ ሃገራዊ ስሜት መዘገባቸው የሚያስመሰግን ተግባር መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ገለጸ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሀመድ ኢድሪስ እንደገለጹት፥ መገናኛ ብዙሃን በስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ ግልጽ፣ ፍትሃዊ፣ ሙያዊ ስነ-ምግባርና መመሪያን የተከተሉ ዘገባዎችን ሲሰሩ ውለዋል።

ጋዜጠኞች መረጃዎችን ለማሰባሰብ በከተማና በገጠር አካባቢዎች ተሰማርተው በተቀናጀ መልኩ ሚዛናዊና ትክክለኛ ዘገባዎችን አቅርበዋል ያሉት አቶ ሙሀመድ፤ “ይህም ጋዜጠኞች መስዋዕትነት ጭምር ለመክፈል ያላቸውን ዝግጁነት ያሳያል” ብለዋል።

ዘገባዎችን ለሕዝብ ተደራሽ ሲያደርጉ በላቀ ሃገራዊ ስሜት እንደሆነ ያስታወሱት ዋና ዳይሬከተሩ፤ ይህ ተግባራቸው በምሳሌነት ሊጠቀስ የሚችል መሆኑንም አብራርተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ መገናኛ ብዙሃኑ በሃገራዊ ምርጫው ላበረከቱት አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርበዋል።

በተመሳሳይ ምርጫውን ለመዘገብ የገቡ የውጭ መገናኛ ብዙሃንም እስካሁን ባለው ሂደት የምርጫውን ዴሞክራሲያዊ ሂደትና ትክክለኛነት የሚያሳዩ መረጃዎችን ለዓለም ሕዝብ አቅርበዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በአንዳንድ የውጭ መገናኛ ብዙሃን በምርጫው አዘጋገብ ላይ የተወሰኑ ችግሮች ቢስተዋልባቸውም በአብዛኛው ግን በመልካም ሊጠቀስ የሚችልና የምርጫ ሂደቱን እውነታ ያሳየ ነበር ነው ያሉት።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.