Fana: At a Speed of Life!

የዘንድሮው ምርጫ ኢትዮጵያ ያሸነፈችበትና መሰረት የሚጥል ነው- አቶ ርስቱ ይርዳ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላለፋ።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ÷ በመላው የክልሉ አካባቢዎች ምርጫው በሰላም መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

የዘንድሮው ምርጫ ኢትዮጵያ ያሸነፈችበትና መሰረት የሚጥል ምርጫ ማካሄድ መቻሉንም ነው የገለጹት።

ህዝቡም ከለሊቱ 11 ፡00 ሰዓት ጀምሮ በምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምፅ ለመስጠት ያደረገው ጥረት እጅግ የሚደነቅና ምስጋና የሚገባው ነው ብለዋል።

ሀገሪቱም ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያካሔደችበት ምዕራፍ የታየበት ታሪካዊ ምርጫ ነውም ሲሉ ገልፀዋል።

በክልሉ ሲወዳደሩ የነበሩ የፖለቲካ ፖርቲዎችም ምርጫው በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አስታውቀዋል።

ከምርጫው በኋላም በዚሁ መንገድ መቀጠል ይገባዋል።

በቀጣይም በሰላምና በልማት ስራዎች ላይ ማተኮር ከሁሉም ይጠበቃል ነው ያሉት።

መራጩን ህዝብ ጨምሮ የፀጥታ ሀይሉ የመገናኛ ብዙሃን የምርጫ አስፈፃሚዎችና በምርጫው ሒደት ሚና የነበራቸው አካላት በሙሉ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

በብርሃኑ በጋሻው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.