Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል የድምጽ አሰጣጡን ሂደት ለማወክ የሞከሩ ሶስት ግለሰቦች ተቀጡ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ፈንቲ-ረሱ ዞን እዋ ወረዳ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን ለማወክ ሞክረዋል የተባሉ 3 ግለሰቦች በእሰራትና ገንዘብ እንዲቀጡ የተወሰነባቸው መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል አሊዲኒ አለሳ ለኢዜአ እንደተናገሩት÷ግለሰቦቹ በእዋ ወረዳ አንድ ምርጫ ጣቢያ ህጋዊ እውቅናና ውክልና ሳይኖራቸው እራሳቸውን የምርጫ ታዛቢ አድረገው በመንቀሳቀስ ሁከት ለመፍጠር ሞክረዋል።

በዚህም  የድምጽ አሰጣጡን ሂደት ለማወክ በመሞከር ጥፋት በቁጥጥር ስር ውለው በአቃቢ ህግ በኩል በፍርድ ቤት ክስ እንደተመሰረተባቸው አስረድተዋል።

በክሱ መሰረትም ጥፋተኝነታቸው በማስረጃ  እንደተረጋገጠባቸው ገልጸው÷ ጉዳያቸውን የተመለከተው የእዋ ወረዳ ፍርድ ቤት ትናንት በዋለው አስቸኳይ ችሎት ሶስቱ ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በአንድ ዓመት እስራትና አንድ ሺህ ብር እንዲቀጡ መወሰኑን አስታውቀዋል።

የፈንቲ-ረሱ ዞን  ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር መሐመድ ይማም በበኩላቸው÷ በወረዳው  ቦለታሞ ቀበሌ አሌዳስኮማ ምርጫ ጣሪያ ላይ አንድ ግለሰብ  “እዚህ ቦታ ምርጫ መካሄድ አትችሉም” በሚል ከሁለት ተባባሪዎቹ ጋር  የድምጽ አሰጣጡን ሂደት ለማወክ በመሞከር ጥፋት በፍርድ ቤት ተከሰው የቅጣት ውሳኔው እንደተላለፈባቸው  ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.