Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በኮንሶ ዞን 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም ተጠናቆ ጊዜያዊ ውጤቶች ይፋ እየሆኑ ነው።

በኮንሶ ዞን ስር ባለ አንድ የምርጫ ክልል በሚገኙ 121 የምርጫ ጣቢያዎች ሀገራዊ ምርጫው በሰላም ተጠናቆ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶች ይፋ መሆናቸውን የዞኑ ምርጫ ቦርድ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ዮሃንስ ጉዮላ እንዳሉት፥ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ሰፊ የህዝብ ተሳትፎና ትብብር የተረጋገጠበት የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ሆኖ ተጠናቋል።

በድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ የቀረቡ ቅሬታዎች በመነጋገር መፈታታቸውን የተናገሩ ሲሆን፥ ለምርጫው ሰላማዊነት የድርሻቸውን ለተወጡ ፓርቲዎችና የኮንሶ ዞን መራጮች ማመስገናቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ በበኩላቸው፥ ምርጫ ውድድር እንደመሆኑ መሸነፍና ማሸነፍ መኖሩን አውቆ የምርጫውን ውጤት በጸጋ ተቀብሎ ወደ ቀጣዩ የለውጥ ምዕራፍ መሸጋገር እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.