Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የተካሄደው ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በአማራ ክልል የተካሄደው ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ÷ በክልሉ የተካሄደው ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን ከደቂቃዎች በፊት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ከጥቃቅን የጸጥታ ችግሮች በስተቀር በክልሉ የተካሄደው ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በሰከነ መንገድ ያለምንም የጸጥታ ችግር መካሄዱን ገልጸዋል።

በቅድመ ምርጫ እና በድምፅ መስጫው ቀን ሰላም ወዳድ ህዝብ አንድም በመምረጥ በሌላ በኩል ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስተዋጿቸው ከፍተኛ ነበር ብለዋል።

የክልሉ የፀጥታ ሀይሎች ከፌደራል ፓሊስና ከመከላከያ ጋር በተቀናጀ መንገድ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በሚገባ ስለተወጡ ምስጋና ሊቸራቸው ይገባል ያሉት ኮሚሽነሩ÷ ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በክልሉ የተካሄደው ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የምርጫ አስፈፃሚዎች እና ተፎካካሪ ፓርቲዎች እገዛ የጎላ ነበር ያሉት ኮሚሽነሩ ከምርጫ በኃላም ትብብራቸው በመቀጠል አለበት ሲሉ ተናግረዋል።

በምርጫ ሂደቱ ህግ የተላለፉ የምርጫ አስፈፃሚዎች እና የፓሊስ አባላት በህግ ቀጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደ ነው ብለዋል ኮሚሽነሩ።

በዳባት ወረዳ አንድ የምርጫ ጣቢያ ተልዕኮ ላይ በነበሩ የፓሊስ አባላት የታጠቁ አካላት በከፈቱት ተኮስ አንድ የፓሊስ አባል ህይወቱ ሲያልፍ ሌላኛው ቆስሏልም ነው የተባለው።

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.